መደመር የተሰኘው ይህ መጽሐፍ የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸላሚና የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የሃገር መምራት ሃላፊነት ላይ ከመጡ በኋላ የጻፉት የመጀመሪያ መጽሐፋቸው ሲሆን፤ በይዘቱም ወቅታዊው የኢትዮጵያ የፖለቲካ መህዳር ሃገር በቀልና አዲስ የፖለቲካ አስተምህሮን ለማስተዋወቅ ታሪካዊ፣ ተግባራዊና አመክኔያዊ ገፊ ምክንያቶች ኢንደሚታዩበት ይሞግታል። እንደ መጽሐፉ የአዲስ ሃገር በቀል ፖለቲካዊ ርዕዮተአለም አስፈላጊነት የሚመነጨው ባለፈው ግማሽ ምዕተ-አመት በሃገራችን ወስጥ ከሌላው አለም እየተዋስን የሞከርናቸው ፖለቲካዊ አስተምህሮዎች የተባለላቸውን ያህል ውጤት ያላመጡበት አንዱ ምክንያት ለኢትዮጵያ ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች እንዲሁም ፖለቲካዊ ምህዳር ባዕድ መሆናቸው እንደሆነ ያስገነዝባል። በመሆኑም ይህን በሃገር ደረጃ የሚታይ በተውሶ ርዕዮተአለም የመዋለል ሃገራዊ ችግር ኢትዮጵያዊ ባህሎችንና ልማዶችን ተንተርሶ ሃገራዊ ችግርን የመፍታት አስፈላጊነትን በማጤን መደመርን እንደ ሃገር በቀልና አዲስ የፖለቲካ ርዕዮተ-አለማዊ አቅጣጫ ያመላክታል።
መጽሐፉ አራት ክፍሎች ያሉት ሲሆን በዓለም ላይ የሚቀነቀኑ የተለያዩ ፍልስፍናዎችን በመዳሰስ ለሀገር በሚጠቅም መልኩ ቁም ነገራቸውን በመቅሰም የራሳችን የምንለው ችግራችንን ሊፈታ የሚችል መላ ማመላከት ላይ እንድናተኩር ይጋብዛል። ለዚህም እንስካሁን የተለመደውን የተነጣጠሉ ትናንሽ አቅሞችን ከመገንባት ባለፈ በመደመር ትልቅ ሃገራዊ ወረት መፍጠርን ያበረታታል።
Medemer is the first book by Nobel Peace Prize awardee and Prime Minister of Ethiopia, Abiy Ahmed since he came to power in 2018. In the book, the prime minister advocates for a fresh, Ethiopian-centric approach to the country's politics, citing the past half-century when previous administrations applied successful ideologies and theories from outside of Ethiopia that failed, being alien to Ethiopian problems and realities. Abiy calls for reversing the trend of importing ideologies for a renewed Ethiopian political ideology that emanates from Ethiopia's social-political context and taps into the country's historical and cultural values.