ይህችን መጽሐፍ ሳዘጋጅ "ሠፈር ትንሿ አገር" የሚለውን እሳቤ እያሰላሰልኩ ነው። ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች አሉባት። ሃብታሙና ድሃው፣ ምሑሩና መሐይሙ፣ ወጥቶአደሩና ሲቪሉ፣ ወጣቱና ጡረተኛው ሁሉ ተጎራብተው ይኖሩባታል። አዎን ሠፈር ትንሿ አገር ናት። ሳሳትመውም ይህንን አንብበን እርስ በእርስም ተናብበን ወደቀደመው ጤናማ አስተሳሰባችን እንድንመለስ ያግዘናል ብዬ ነው። "ታምሜአለሁና እጅጉን በጠና፤ ሐኪሞቹ ሠፈር ውሰዱኝ ቀበና" ተብሎ የተገጠመልን አይደለን?