የብሔርተኝነት ፖለቲካዊ ኤኮኖሚ (Ethnic Political Economy)
Book

የብሔርተኝነት ፖለቲካዊ ኤኮኖሚ (Ethnic Political Economy)

(Write a Review)
Hardcover
$44.95
የአገራችን ኤኮኖሚ ፈጣን ዕድገት አላቸው ተብለው ከሚገመቱት ውስጥ ቢሆንም ለሕዝብ እርካታን፣ ለመንግሥት እረፍትን፣ ለኤኮኖሚ ባለ ድርሻዎችም የሚያጠረቃ ትርፍና ዕድገትን አላመጣም። ይልቁንም፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአምራቹም ሆነ የተጠቃሚው እጅ እያጠረ መጥቷል። ይህንን ለማሻሻል አገር በቀልም ሆነ በውጭ መንግሥታትና ድርጅቶች ጫና የሚወሰዱ እርምጃዎች ችግሩን ከማባባስ ባሻገር መፍትሔ ሊሆኑ አልቻሉም።

የአገራችን የብሔር ፖለቲካ በኤኮኖሚው ላይ ምን ዓይነት ሚና ይጫወታል? ለመሆኑ ብሔርተኝነት ምንድር ነው? ብሔርተኝነትና ዘረኝነት አንድነታቸውና ልዩነታቸው ምንድር ነው? የኤኮኖሚው ሁኔታ ለብሔር ፖለቲካው ገበያ መድራት ምን አስተዋጽዖ አድርጓል?

ይህ መጽሐፍ የተቀረጸው መደበኛ የኤኮኖሚክስም ሆነ የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት ያልወሰዱ፣ ነገር ግን በኢትዮጵያ ኤኮኖሚና ፖለቲካ ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ የሚሹ ሰዎችን ታሳቢ በማድረግ ነው። በተለይም ሊካሄድ በታሰበው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ የሚሳተፉም ሆነ አሳብ በማመንጨት የሚታደሙ ሊጠቀሙበት ይችላሉ በሚል መነሻ ተጽፏል። ነገር ግን ለኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችና መምህራንም ማጣቀሻ በሚሆን መልክ ተዘጋጅቷል።

የመጽሐፉ መነሻ ግምት በብሔርተኝነት የታጠረው ፖለቲካችን በኤኮኖሚው ዕድገትና አገራዊ ለውጥ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አለው የሚል ነው። ይህ ተጽዕኖ ምን ይመሥላል? አሉታዊ ወይስ አዎንታዊ? ምንስ ያክል ነው? ይህን መላ ምት በተለያዩ የኤኮኖሚ ዕድገት መለኪያዎች፣ ተጨባጭ ምክንያቶችና ምሳሌዎች ለመለካት ተሞክሯል። ብያኔው ምን ይሆን?

መጽሐፉ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ባለሙያዎች ስለ ብሔርና ዘረኝነት፣ ስለ ኤኮኖሚ ፖሊሲ አወጣጥ፣ ስለ ኢትዮጵያ ኤኮኖሚና ፖለቲካ የተጻፉ በርካታ መጻሕፍትን ዋቢ ያደርጋል። በመንግሥትና በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተቀባይነት ያ
Hardcover
$44.95
© 1999 – 2024 DiscountMags.com All rights reserved.